እግዚአብሔር ለህዝበ እስራኤል ያደረገው ነገር ድንቅ ነው። በባርነት ቀንበር ከነበሩበት ስፍራ በበረታች እጁ አወጣቸው። ቀን የሀሩሩ ፀሃይ እንዳያቃጥላቸው በደመና፣ ማታ ደግሞ የሌሊቱ ቆፈን እንዳይበርዳቸው በእሳት አምድ መራቸው። ነገር ግን የብዙሃኑ መልስ የቀና አልነበረም። ለእግዚአብሔር ታዛዥ ከመሆን ጎደሉ። በራሳቸው ምኞትና ሀሳብ ለመጓዝ መረጡ። እግዚአብሔርም ለልባቸው ሀሳብ አሳልፎ ሰጣቸው። “እንደ ልባቸው ሥራ ተውኋቸው፥ በልባቸውም አሳብ ሄዱ።” መዝ 81፥12
በማለት እግዚአብሔር ተናገረ።
👉 “በህይወትህ የምትፈራው ነገር ምንድን ነው?” በማለት ለራሴ ጠየኩት። “የእግዚአብሔር አብሮነት ቢለየኝ ምን ይውጠኝ ይሆን” በማለት ሳስብ ራሴን አገኘሁት። ይህ እጅግ የሚያስፈራና የሚያስደነግጥ ነገር ነው። እግዚአብሔር አብሮነት ከሌለን ህይወታችን ትርጉም የሌለው ባዶ ነው የሚሆነው።
👉እግዚአብሔርን እንዲህ እለዋለሁ:- እግዚአብሔር ሆይ ለልቤ ሀሳብ አትተወኝ።
በራሴ መንገድ እንድጓዝ አትተወኝ።
አምላኬ ሆይ፣ ለፈቃዴ አሳልፈህ አትስጠኝ።
አንተ ከተውከኝ እጠፋለሁና እጄን አጥብቀህ ያዘው።
ሰው ነኝና ድንገት ከእቅፍህ ለመውጣት እዳዳ ይሆናል ነገር ግን አትተወኝ።
ከአንተ እርቄ ብሄድ እንኳን ቸርነትህና ምሕረትህ በህይወቴ ዘመን ሁሉ ይከተለኝ።
የመንፈስህ ማደሪያ ቅዱስ ስፍራ አድርገህ ስራኝ።
አምላኬ ሆይ፣ ፍቅርህን በመግፋት ስንት ጊዜ ኮብልዬ ሄድኩኝ?
በአንተ ላይስ ተረከዜን ስንቴ አነሳሁኝ?
አቤቱ፣ ይቅር በለኝ።
ስጋ ደካማ ነውና ለልቤ ፈቃድ ደግሞ አሳልፈህ አትስጠኝ።
እባክህ ለሀሳቤ አትተወኝ🙏
አስተያየት ያስቀምጡ