ደህና ነኝ
ሃዘኔን፣ ችግሬን፣ ብሶቴን ደብቄ ፣
ህመሜ እንዳይታይ በጣም ተጠንቅቄ፣
የአፌን ጥጋጥግ የግዴን ፈልቅቄ፣
በውሸት ፈገግታ ለይስሙላ ስቄ፣
ሌሎች እንዳያዩት የውስጤን አምቄ፣
ያልለመደበትን እየሳቀ ጥርሴ ፣
ለሚጠይቅ ሁሉ ” ደህና ነኝ” ነው መልሴ።
ደህና ነኝ
ሃዘኔን፣ ችግሬን፣ ብሶቴን ደብቄ ፣
ህመሜ እንዳይታይ በጣም ተጠንቅቄ፣
የአፌን ጥጋጥግ የግዴን ፈልቅቄ፣
በውሸት ፈገግታ ለይስሙላ ስቄ፣
ሌሎች እንዳያዩት የውስጤን አምቄ፣
ያልለመደበትን እየሳቀ ጥርሴ ፣
ለሚጠይቅ ሁሉ ” ደህና ነኝ” ነው መልሴ።
Leave a comment