ከሀገሩ ወጥቶ የሚኖረው ወጣት

Published by

on

ከሀገሩ ወጥቶ የሚኖር አንድ ወጣት ልጅ ነበር። መቼም የሰው ልጅ መገናኛው ብዙ ነውና ይህ ልጅ ከአንዲት እንስት ጋር ይተዋወቃል። ግንኙነታቸውም አንድ ሁለት እያለ እየጠነከረ መጣ። ወዳጅነታቸው ጠበቀ። ታዲያ በዚህ መሃል ልጅቷ እርሷ ጋር የፍቅር ስሜት እንዳለና እርሱ ምን እንደሚያስብ ትጠይቀዋለች። ልጁም ደስ እንደምትለው በመጥቀስ ነገር ግን ጊዜ እንደሚፈልግ ይነግራታል። ግና እርሷ ልቧ ሊያርፍ እንዳልቻለና የሕይወት አጋሯ ይሆን ዘንድ በድጋሜ ትጠይቀው ጀምር። እርሱም አንድ ቅደመ ሁኔታ እንዳለውና ከዛ በኃላ የመጨረሻ ውሳኔውን እንደሚያሳውቃት በፍቅር ቃል ምላሹን ይሰጣታል። ቅድመ ሁኔታውም ሀገር ቤት ሲሄድ በአካል ተገናኝተው ያለውን ነገር በደንብ አጢነው ለመወሰን ነበር። ነገር ግን ከጊዜ በኃላ እርሷ ጋር ያለው ስሜት እየቀነሰ የመጣ መሰለው። ለትንሽም ጊዜ ሳይነጋገሩ ቆዩ። ለካስ እርሷ በመሃል ስራዋን ስትሰራ ነበርና እንደምታፈቅረው በነገረችው በወራቶች ልዩነት ውስጥ የሌላ ሰው ሙሽራ ሆና አረፈችው።

👉ብዙ ሰዎች አፋቸውና አንደበታቸው ለየቅል ነው። ምላሳቸው የሚያወራው ሌላ፣ በውስጣቸው የሚያደርጉት ሌላ። አራንባና ቆቦ! እነዚህ ሰዎች ውጫቸውና ውስጣቸው ፍፁም የተለያየ ነው። “!” ብለው ባሞገሱበት ምላሳቸው ሌላ ሰው ጋር በመሄድ “!” በማለት ለማኮሰመን ቀስቃሽ አያሻቸውም።

በቅዱስ ቃሉ ውስጥ

👉እስራኤላዊያን ወደ ከነዓን ምድር በሚያደርጉት ጉዞ ላይ ለእግዚአብሔር የተመቹ ህዝቦች አልነበሩም ነበር። “ታጥቦ ጭቃ!” እንደሚል ተረቱ ለኃጢአታችው ንሰሃ በገቡበት ቅፅበት የእሮሮን ጩኸት ያሰማሉ። “በአፋቸው ብቻ ወደዱት፤ በአንደበታቸውም ዋሹበት፤”

መዝ 78፥36

👉ብዙዎቻችን ከእስራኤላዊያን ጋር ተመሳሳይነት ያለውን ህይወት እንመራለን። ከተግባር ይልቅ ወሬን የምናስቀድም አፋዊያን ነን። የአፍ ሰዎች! ይህ ሊወገድ የሚገባው መጥፎ ማንነት ነው። አፋችንና አንደበታችን አንድ ይሁን። ያወራነውን እንኑረው። የሰበክነውን እንተግብረው። ያነበብነውን እንመስከረው።

👉እግዚአብሔርን እንዲህ እለዋለሁ:- አምላኬ ሆይ፣ የኃጢአቴ ብዛት እኔን ከመውደድ ስላላገደህ አመሰግንሃለሁ።

ውስጤንና ውጬን አንድ አይነት አድርገው።

የማወራውን እንድኖረው በፀጋህ እርዳኝ🙏

አስተያየት ያስቀምጡ

Discover more from Edudream Family Community

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading