ሶሥት የማይተዋወቁ የሚመስሉ ሰዎች

Published by

on

አንድ ቀን ወደአዲስ አበባ ለቼክ አፕ ሄጄ ነበር ግን አዲስ አበባ በጥሩ ስነምግባር ባላቸው ልጆች ተቀብላኛለች! ከወልቂጤ ወደ አዲስ አበባ ባቀናውበት ጊዜ የሚያስፈልጉ መረጃዎችን አልያዝሁም ነበር፣ ወረፋ ለመያዝ በምናደርገው ዝግጅት፣ አንዱ አስተናጋጅ “እሪፈር ያልዛያዛችው አትስተናገዱም!” አለ፣ እንደዛ ሲል ግራ በመጋባት እሪፈር ወረቀት አሁን የት ነው የሚገኘው  አልኩኝ? አንዱ ከአጠገቤ ልክ እንደኔ ግራ የተጋባ በመምሰል፣ “እኔም እኮ አልያዝሁም” አሁን እንዴት ነው ወንድሜን ሳላሳክም የምሄደው” አለ፣ በዚህ አጋጣሚ ከሰውየው ጋር በመጨነቅ ከሰልፋችን ወተን ስለጉዳዩ በማውራት ላይ እያልን አንድ ሰዉ በአጋጣሚ የሰማ በመምሰል ” እሪፈር የሚሰጡ በሩጋ ወጣ ብትሉ ታገኛላችው!” አለን!። ሁለታችን ተያይዘን ወጣን፣ ወተን ትንሽ እንደተጋዝን አንድ ሰው ወደሆስፒታሉ ወረቀት በመያዝ በፍጥነት የሚሄድ ሰው አገኘን፣ አብሮኝ ያለው ሰው “እስኪ ይህ ሰው የሚያውቀው ከሆነ እንጠይቀው” አለኝ፣ እኔም ተስማምቼ እሺ አልኩት፣ እሱም ቀረበና” ወንድሜ እሪፈር የሚፅፍ ከዚህ አካባቢ አለ ተብለን ነበር፣ ካወቅክኽው ልታሳየን ትችላለህ” አለው፣ እሱም ” አወ እኔ እራሱ ከዛ ቆይቼ ነው ከደረስን እንሂድ ግን ሶስት ሰሀት ነው የሚዘጋው” አለን። ከዛም ተያይዘን መሄድ ጀመርን….ከሱ ከበሩ ነው የተባለው ቀርቶ 1.5km የሚሆን ተጓዝን….ከዛ በሃላ እሪፈር ይሰጣል የተባለውን ሰው ሱፉን ሽክ ብሎ ለብሶ ሲሄድ አገኘነው፣ ያ አብሮን የነበረው ሰው “ዎዎዎዎ!! ቢሮውን ዘግቶ እየወጣ ነው ያውኖት!!” አለ። ያ መጀመሪያ አብሮኝ የነበረው ሮጦ ሄደና ” ጌታዬ እሩቅ አገር ነው ወንድሜን ይዤ የመጣውት፣ እሱን ሳላሳክም አልመለስም እባክህ እርዳኝ” ብሎ እግሩ ስር ወደቀ። ሰውዬውም “እስከዛሬ አታውቁም እንዴ እሪፈር መስጠታችን ግን ሶስት ሰሀት ነው የምንዘጋው ለዛሬው ችግር የለም ለወደፊቱ ግን ቀደም ብላችሁ ነው መምጣት” ብሎ ተያይዘን ምንገዳችን ቀጠልን። ትንሽ እንደተጓዝነ “በሉ ሁለታችሁ እዚህ ነው የምትጠብቁ እኔ አንዱን ይዤ እሄዳለው ግን ምንም አይነት ብርም ሆነ ስልክ አትያዝ ከትኬት መውጫ ሁለት ብር በቀር” አለ። አንዱ የያዘውን ገንዘብ ለኔ አስረክቦኝ ሄዴ። ትኬት የሚመስል ስማችን የምንፅፍበት ወረቀት ለሁላችን ተሰጠን ከዛ ላይ ስማችን ፃፍንበት፣ከዚያም ከመካከላችን አንዱ የያዘውን ገንዘብ፣ በብዙ መቶ ኖቶሽ የሚቆጠር ብር እና ስልኩን ለኔ አስረክቦኝ ሄዴ። ከሄደ ከ አምስት ደቂቃ በሃላ ሰውየው ሌላ ተረኛ ለመውሰድ መጣ፣ ለልጁ ንብረቱን በመመለስ እኔን በተራዬ ለመውሰድ መጣ፣ ከዛም እንደተለመደው ያለኝን ሁሉ በመስጠት፣ ለትኬት መቁረጫ ሁለት ብር ብቻ በመያዝ ለመሄድ ተነሳው፣ ትንሽ እንደተጋዝን “ትኬትህን ስጠኝ” አለኝ። አብሮኝ የነበረው ትኬቴን ይዞት ነበር፣ ሳልቀበለው እረስቼ ሄድኩኝ፣ ለሰውዬውም ጋደኛዬ ነው የያዘው አልኩት እሱም ” እንዴት ሳትይዝ ትመጣለህ ሂድ ተቀበለው” አለኝ፣እኔ ከዚህ ልጠብቅህ አለኝ፣ ስመለስ ሰዎቹ የሉም፣ እኔም ያኔ ገባኝ እነዚ የማይተዋወቁ የሚመስሉ እሶስት ሰዎች ይተዋወቃሉ፣ አንዱ ንብረታቸውን ጠባቂ፣ ሁለተኛው ሰውን የማመን ምሳሌ በማሳየት እና ሶስተኛው ስራ አስፈፃሚ በመሆን ጎል ማስቆጠር ችለዋል። 

አስተያየት ያስቀምጡ

Discover more from Edudream Family Community

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading