ሁላችንም ዘውትራዊ የሆነ የልብ መሻት አለን። አንደኛውን ቀን ሸኝተን ሌላኛውን ስንቀበል ከትላንቱ ይልቅ ምኞታችን ላይ እንቀርባለን። ጣፋጭ የሆነችው የማለዳ ፀሃይ ይህንን መልካም ዜና በየጠዋቱ ታበስረናለች። ነገር ግን ሰርክ እንዳሰብነው ሁኔታዎች ላይሄዱ ይችላሉና ቀን ሲጎድል ልብ ይከዳል። ስሜት ከራስ ጋር ተፋቶ ባዶነት ይነግሳል። የሌሊቱን ማለቅ የምታበስረው የፀሃዮ ፍንጣቂ ውስጣችን ያለውን ድቅድቅ…