አንደኛውን መከራ አለፍኩት ስል ሌላኛው ተሽቀዳድሞ ይመጣብኛል ። የውድቀት ታሪኬ አልቆ ስኬቴ መጣ ብዬ ሳልጨርስ የጨበጥኩት ነገር ከእጄ ይበተንብኛል። ሰውኛ ፍቅርን አገኘው ብዬ ጮቤ ስረግጥ “ፍ-‘ቅር’” ሆኖብኝ እኔ ጋር የመጣ የመሰለኝ ነገር እዛው ባለበት ይቀራል። ልቤ ፍስስ ብሎ ያውቃል። ስጋ ለብሰው በአካል የመጡ ነገሮች ህልም እንዲሆኑ ተመኝቼ አውቃለሁ። እምነቴን ሰጥቼ…