ምድብ፥ ሠው ነኝ እና ከወደቅሁኝ የምደገፈው ሰው ነው።
-
ሠው ነኝ እና ከወደቅሁኝ የምደገፈው ሰው ነው።
ወደቅሁኝ ሲለኝ አልደገፍኩትም፣ እራስ ወዳድነቴን አሳየውት፣ እርቦት አይቸው ከምሰጠው ይልቅ፣ ከንፈሬን መጠጥሁኝ። ኪሴ ሆዳም ሆኖ ምንም የለኝም ተምሯል፣ ከትናንትናው ዛሬ የተሻለ አቅም ቢኖረውም የለኝምን ማለትን ስለለመደ አሁንም የለውም። አይ ሰው ሰውነቴ፣ ለሰዉነቴ ያልሆነ፣ ሰውነትን ትቶ ጭካኔን የተማረ፣ የህሊናን ጥያቄ እንደሚመቸው የሚመልሥ፣ በራስ ወዳድነት ለዘመናት የሚገዛ፣ ህሊና ተጨፍልቆ ሥልጣኑን ተቀምቶ በሆድና…