አንተ ያልከው ይሁን…

Published by

on

ሰውየው አስር ክፍል ቤት ሠርቶ ብቻውን ሲኖር አንድ ቀን በሩ ተንኳኳ ሲከፍት ጌታ ነው፡፡ “ውይ አምላኬ ጌታዬ አንተ እኔ ቤቴ መጣህ?” ብሎ በደስታ ተቀብሎት አንድ ክፍል ቤት ሰጥቶት መኖር ጀመሩ፡፡በሌላ ጊዜ በሩ ተንኳኳ፣ ሲከፍት ሰይጣን ነው፡፡ ተበሳጭቶ ይዘጋና “ጌታዬ ሆይ አንተ እኔ ቤት እያለህ ሰይጣን የእኔን ቤት እንዴት ያንኳኳል?” አለው፡፡

ፈጣሪም “ቤቱ የአንተ እንጂ የእኔ አይደለም ” አለው፡፡ ሰውየውም ተሰምቶት ሁለት ክፍል ቤት ለፈጣሪ ጨምሮለት እርሱ ሰባት ክፍል ይዞ መኖር ቀጠሉ፡፡ በሩ ተንኳኳ ሲከፈት ሰይጣን ነው፡፡ ተበሳጭቶ ይዘጋና “ጌታዬ ሆይ አንተ እኔ ቤት እያለህ ሰይጣን የእኔን ቤት እንዴት ያንኳኳል? ” አለው፡፡ ጌታም ” ቤቱ የአንተ እንጂ የእኔ አይደለም ” አለው፡፡

_ሰውየውም ተሰምቶት ከፈጣሪው ጋር እኩል ለእኩል ተካፈለ፡፡ነገር ግን ቤቱ ከቀድሞ ይልቅ ተንኳኳ ፡፡ አዝኖም ይዘጋና ጌታ ሆይ አለው፡፡ፈጣሪም የቀድሞውን መልስ ሰጠው፡፡ በዚህ ጊዜ ሰውየው ለራሱ አንድ ክፍል ቤት ይዞ ዘጠኙን ክፍል ቤት ለጌታ ሰጠው፡፡ ነገር ግን ከቀድሞው ይልቅ በጣም ተንኳኳ፡፡ ቢከፈት ሰይጣን ነው፡ በሩን ይዘጋና ወደ ፈጣሪ ሄዶ ” ፈጣሪየ ሆይ ምሥጢሩ ምንድን ነው? ” አለው፡፡ “ፈጣሪ ግን ቤቱ የአንተ እንጂ የእኔ አይደለም “አለው፡፡ በዚህ ጊዜ ዐሥሩንም ክፍል ለፈጣሪ አስረከበ፡፡

_ፈጣሪም አንድ ክፍል ቤት ለሰውየው ሰጠው፡፡ በሩም ተንኳኳ ፈጣሪም ሊከፍት ተነሣ፡፡ ሲከፍት ሰይጣን ነው፡፡ ሰይጣንም ” ይቅርታ የአንተ ቤት መሆኑን አላወቅሁም ” ብሎ ሄደ፡፡ ከዚያን ቀን ጀምሮ መንኳኳት ቆመ፡፡በእኛም ህይወት እንድሁ ነው።ሁሉንም የሕይወታችንን ክፍል

ለእግዚአብሔር ካላስረከብን መንኳኳቱ አይቆምም፡፡ 1ዐ% ስንሰጥ ይንኳኳል፡፡ 30% ስንሰጥ ይንኳኳል፡፡ 50%ስንሰጥ ይንኳኳል፡፡ 99% ስንሰጥ ይበልጥ ይንኳኳል፡፡ 100% ስንሰጥ መንኳኳት ይቆማል፡፡

__ እኛ ከከፈትን ሰይጣን ይገዳደረናል፡፡ፈጣሪ ሲከፍት ሰይጣን ” ይቅርታ የአንተ ቤት መሆኑን አላወቅሁም “ብሎ ይሄዳል፡፡ፈጣሪ ሰማይን የደስታ አገር ያደረጋት ሙሉ በሙሉ የፈጣሪ ፈቃድ የጸናባት በመሆኗ ነው፡፡ባንተም ሕይወት የሰማይ ደስታ የሚመጣው የፈጣሪ ፈቃድ በሕይወትህ ሙሉ በሙሉ ሲፈጸም ነው፡፡ ስለዚህ፡-ፈጣሪን እረኛህ አድርገው፡፡ በፍጹም ልብህ ተከተለው፡፡የሚያስፈልጉህ ነገሮችም አንተን ይከተሉሃል፡፡ሙሉ ሕይወታችንን ለእግዚአብሔርእናስረክብ።”

እግዚአብሔር ማስተዋልን ጥበብን እውቀትን ከፍቅር ጋርይስጠን አሜን እግዚአብሄር ብረሃኔ እና መድሀኒቴ ነው!

አስተያየት ያስቀምጡ

Discover more from Edudream Family Community

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading