ባልነቃ ህሊና መኖር የሚያመጣው ጣጣ፣ ዝምብሎ መኖር ግራና ቀኝ ሳያዩ ኑሮን ብቻ መኖር፣ በዙሪያህ ያለውን ሰው አለመመልከት፣ ምን ያስከፋቸዋል ምን አያስከፋቸውም ብሎ አለማሰብ የሚያስከትለውን ጉዳት በህይወትህ ሳታስብ አትኑር። ግራ እና ቀኝ ተመልከት አንድን ነገር ከማድረግህ በፊት ወይም ካለማድረግ በፉት ሌላ ሰው ምን ያስባል ብለህ አስብ ያን ነገር ባለማድረግህ ወይም በማድረግህ ሌላ ሰው በጣም ሊቀየም ይችላል ብለህ ማሰብ አንተን ከሌሎቹ ሰዎች ልዩ ያደርግሀል:: ልዩ ለመሆን አስቀድመህ መተምበይ አለብህ ስትተነብይ ብዙነገሮችን ማየት ትችላለህ:: ሳትተነብይ አትኑር እንደዛ ከሆንህ ሀይምራቸው ካልነቃው ከእንሰሳ አንለይም::የተነበይኸው እና ወደፊ የሆነውን መዝን ምን ያክል አንተ ካሰብኸው ጋር ተቀራርባል በዚህ ሁኔታ ወደፊት የሚፈጠርብህን ክፍተት ማጥበብ ትችላለህ:: መኖር ማለት ብቻን ሳይሆን ከሰው ጋር ነው፣ ለመኖር ለሌላ ማሰብ ግድ ነው፣ ካላሰብህ አብሮህ የሚኖር ታጣለህ:: ሁሉም ነገር ሰው ሲኖር ያምራል፣ ሰው በሌለበት ምን የመሰለ ዘመናዊ ልብስ ብትለብስ ብታጌጥ ትርጉም የለውም ሰው ባለበት መኖር ማጌጥ የምትችለው በዙሪያህ ስላለው ሰው ስታስብ ነው:: ማር ማር መሆኑን የምታውቀው ስትቀምሰው ነው እንዲሁም መራራ መራራ መሆኑ የሚታወቀው ሲቀመስ ነው፣ከሰው ጋር አለመኖር የራሱ የሆነ መራራነት ስላለው አብረውዋችው ለሚኖሩ ሰዎች በሚገባ ጥንቃቄ አድርጉ::
አስተያየት ያስቀምጡ