አንደኛውን መከራ አለፍኩት ስል ሌላኛው ተሽቀዳድሞ ይመጣብኛል ። የውድቀት ታሪኬ አልቆ ስኬቴ መጣ ብዬ ሳልጨርስ የጨበጥኩት ነገር ከእጄ ይበተንብኛል። ሰውኛ ፍቅርን አገኘው ብዬ ጮቤ ስረግጥ “ፍ-‘ቅር’” ሆኖብኝ እኔ ጋር የመጣ የመሰለኝ ነገር እዛው ባለበት ይቀራል።
ልቤ ፍስስ ብሎ ያውቃል።
ስጋ ለብሰው በአካል የመጡ ነገሮች ህልም እንዲሆኑ ተመኝቼ አውቃለሁ። እምነቴን ሰጥቼ ክህደትን ተቀብዬም አውቃሉ።
ስሜቱ እንዲሁ በቃል የሚገለፅ አይደለም። “እ…ህ…ህ”…”እ…ዬ…ዬ” ብየ እንኳን ልረሳቸው የማልችላቸው የልብ ህመሞች ሆነውብኛል።
እግዚአብሔር ግን የውስጤ ሰላም፣ የልቤ እረፍት ነው።
በእነዚህ እጅግ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ሳልፍ ብቻየን ጥሎኝ ሊሄድ ከቶ አልተነሳም።
ካጠገቤ በመሆን “ቀኝ እጄን ” ላይለቀኝ ይዞኛል።
በቅዱስ ቃሉ እንዲህ ሲል ተናግሯል:- “እኔ ግን ዘወትር ከአንተ ጋር ነኝ፥ ቀኝ እጄንም ያዝኸኝ።” መዝ 73፥23
“እርሱን አጥብቀው የያዙ እጆች ከቶ አያፍሩም።”
🛐ፊትህም ስቀርብ ፀሎቴ:- ቸሩ አምላኬ ሆይ በከበደኝ ቀኔ ላይ ደርሰህ የማያልፍ የሚመስሉኝን ከባባድ ወቅቶች ስለምታሳልፈኝ አመሰግንሃለሁ ።
አምላኬ ሆይ፣ በወደቅሁ ሰዓት ቀኝ እጄን ይዘህ ስላቆምከኝ አከብርሃለሁ። ዘውትርም ደግሞ ከአንተ ጋር እንድሆን በፀጋህ እርዳኝ።
አሜን🙏
አስተያየት ያስቀምጡ