አንድ ቀን በቆምኩበት መቶ አንድ ሰው “አባቴ በጣም ተቸገርኩኝ” ይላል። እኔም በሀሳብ ጭልጥ ብዬ ከራሴ ጋር ስላልነበርኩኝ መልስ አልሰጠውትም ነበር፣ ትንሽ ቆየና የሱሪየን ጫፍ በመንካት “ዳቦ የምገዛበት አንድም ብርም ቢሆን ስጠኝ አለኝ”። እኔም ልብሴን በመጎተቱ ምክኒያት ወደቀልቤ ስለተመለስኩኝ ወዳውኑ ወሬ ማውራት ጀመርን። ምን ነበር ያልከኝ? አልኩት። እሱም “ከነጋ ምንም እህል አልቀመስኩም!” አለኝ። ታዳ እኔ ይህን በመስማቴ አሁን ምን እንዳደርግልህ ነው የምትፈልገው? ብዬ ጠየቅሁት። እርሱም “ከነጋ ምንም እህል አልበላውም የዳቦ መግዣ ስጠኝ” አለኝ እኔም ዳቦ የምትፈልግ ከሆን እኔ ልግዛልህ ና? አልኩት” እርሱም “ብሩን ስጠኝ እኔ እራሴ እገዛለው” አለኝ። ለዳቦ መግዣ የሚሆን ሰጠውት፣ እርሱም እንዳለው ዳቦውን ገዛ መብላትቱን ከመጀመሩ በፊት አይኖቹን ወደላይ በማድረግ ጌታውን ማመስገን ጀመረ እንዲህ በማለት “ጌታ ሆይ አንተ የከፈትከውን ጉሮሮ ሳትዘጋ አታድርም ወፎችን እንደምትመግብ እኛን ልጆችህንም ትመግባለህ ለሁሉም ሰጭ አንተ ነህ ለልጆችህም መስጠትን ስላስተማርክ አመሰግንሀለው” ብሎ አመሰገነ። እኔም በልጁ በሚያመሰግንበት ግዜ በጣም ስለተመሰጥሁኝ የምሄድበትን እስከመርሳት ድረስ ማዳመጥ ጀመርኩኝ። የሰው ልጅ ጌታውን ለማመስገን ያለበት ቦታ ዐይወስነውም በዝቅታም በከፍታም እግዛቤሔር ይመሰገናል። ግን ግዜ ጠብቀን ኑሮአችን ስሰመር የተሳካልን ሲመስለን አይደለም፣ ምንም በሌለን ሰሀትም እርሱን እናመስግን። እስኪ ስንቶቻቺን ነን በሌለንም ነገር ላይ የምናመሰግነው እንዲሁም የተሰጠንን ነገር ብቻ በመቁጠር እግር/ርን ከማመስገን ይልቅ ያልተደረገልነን ነገር በመቁጠር ሁሌ የምናማርረው ስንቶቻችን ነን? ይህን ሰው በምናይበት ጊዜ በተሰጠው በአንድ ቀን ዳቦ እንደዚህን ካመሰገነ፣ እኛስ ስንት ነገር ተደርጎልን እንዴት አድርገን ነው እግ/ርን የምናመሰግነው?
አስተያየት ያስቀምጡ