እኔ ማን ነኝ

Published by

on

አንተ ማለት ሰው ነህ በእግዛቤሔር አምሳል የተፈጠርህ ።ሳዩህ የምታስፈራ የእግዚአብሔር/ር ክብር የሚገለጥብህ የርሱ አምሳያ የሆንህ በምድር ላይ እርሱን የምትወክል አንተ ሰው ነህ ። የሰው ልጅ ማንነት በቢሄሩ፣ በከለሩ፣ወይም በሚኖርበት አካባቢ አይደለም የሚታየው ግን የሰው ልጅ በሰውነቱ ነው መታየት ያለበት ።ሰው ማለት አዳም ማለት ነው እርሱም የሁሉ አባት ማለት ነው በእግ/ር እጆች የተቀረፀ በእርሱም ህያው እስትንፋስ ህይወት ያገኘ እርሱ ነው ሰው ሁላችንም የርሱ ልጆች ነን። ይህ ማለት ሁላችን አንድ ሰው በርሱ በአዳም የተወለድን ስንሆን እርሱም ደግሞ የእግዚአብሔር አምሳል ማለት ፣ነዉ ስለዚህ እኔ ማን ነኝ ለሚለው አንተ የእግዚአብሔር አምሳል  ነህ። ለምሳሌ ያክል በሰው ፊት ቆሞ መናገር የሰው ልጅ በአምላክ አምሳል ስለተፈጠረ ስለምንፈራ የያዝነው እንናገራለን ወይም ማስተላለፍ የምንፈልገው መልክት ማስተላለፍ እስከሚሳነን ድረስ እንፈራለን  ይህም የሚያሳየው በሰው ፊት መቆም ማለት በእግዚአብሔር አምሳል ፊት መቆም ስለሆነ ነው በጣም የምንፈራው ። ነገር ግን የሰው ልጅ ሰው ከሆነበት ደረጃ ሲወርድ  እና ሰውነቱን ሲጥል የእግዚአብሔር አምሳል መሆኑን እና ክቡር መሆኑን ሲዘነጋ በሰዉ ልጅ መከበሩ መፈራቱን ያጣል። ይህም የሚሆነው እግዚአብሔር የማይከብርበትን ነገር ሲሰራ ሰው መሆኑን  እረ ስቶ ማሰብ ሲሳነው እና የሚያደርጋቸው ነገሮች ነገሮች ሁሉ በራሱ የህሊና ዳኛ ያልተዳኙ ሲሆን የሚሰራቸው ነገሮች ደመነብሳዊ ሲሖኑ ያ ሰው ከሰውነት ተራ ወረደ ማለት ነው።

አስተያየት ያስቀምጡ

Discover more from Edudream Family Community

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading