ተስፋ የመኖር ሚስጢር

Published by

on

ተስፋ ካለን ለመኖር ሀይል አለን የምናስባቸው ነገሮች እንድሚከናወኑልን አድርገን እናስባለን። ለመኖራችን ትልቅ ስንቅ በመሆን ልክ እንደ ነዳጅ እንድንቀሳቀስ የሚረዳን ነው። አንድ መኪና ወይም ማንኛውም ሞተር በቂ የሆነ ነዳጅ ከሌለው እንደማይንቀሳቀስ ሁሉ የሰው ልጅም ወደፉት እንዲኖር የሚያደርገው ተስፉ ከሌለው ሊኖር አይችልም፣ ተስፋ የመኖራችን ሚስጢር ወደፉት እንድንጓዝ የሚያደርገን የህይወታችን ነዳጅ ማለት ነው። ተስፋ ከሌለን ለመኖር በጣም አስቸጋሪ በጨለማ ውስጥ ካለብርሀን መጓዝ ማለት ነው፣ ስለሚሰለቸን ከመጓዝ እንታገዳለን። ለምሳለሌ ያክል የእስራኤልን ህዝብ ከግብፅ ወደከነአን በሚጓዙበት ጊዜ አርባ ቀን የሚጓዙትን አርባ አመት በሚጋዙበት ጊዜ ወደተገባላቸው ሀገር እንደሚገቡ ተስፋ ስለነበራቸው ጉዟቸውን አላቆሙም። በምንኖርበት ጊዜ ይሆንልናል ብለን ተስፋ ያደረግናቸው ነገሮች በራሳችን በተለያዩ ነገሮች ማከናወን ካለብን ጊዜ ትንሽ ሊዘገይ ይችላል፣ ለምሳሌ ያክል ምሬት፣ መሰላቸት፣ አሁን ካለን ይልቅ ወደሃላ ማሰብ እና በምንጋፈጣቸው ችግሮች ፈጣሪን ማማረር፣ እነዚህ ሁሉ እስራኤል በጉዞአቸው ከአርባ ቀን ወደ አራት መቶ አመት እንደሆነባቸው በኛ ላይም እንዲሁ በፍጥነት ተስፋ አድርገን ልንደርስባቸው ካሉት ስኬቶቻችን ወደሃላ ሊጎትተን ይችላል። ስለዚህ ተስፋ የመኖራችን የእጅ መብራት የኑራችን ውል ሲጠፋን ውሉን አይተን የተቋጠረውን የህይወታችን ቋጠሮ የምንፈታበት ስለሆነ በህይወታችን ውስጥ ተስፋ መቁረጥ የለብንም።

አስተያየት ያስቀምጡ

Discover more from Edudream Family Community

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading