በሀሳባችን ክፉ ሀሳብ የሚመጣብን ከሆነ እንቃወመው፣ ግዜ አንስጠው። ከክፉ ሀሳባችን ቶሎ ብለን መውጣት አለብን፣ ክፉ ሀሳብ መርዝ ማለት ነው በውስጣችን ከቆዬ ሁሉ ነገራችን መመረዝ የሚችል እና በውስጣችን ያለውን መልካም ነገር የሚገድል እንዲሁም የሚያጠፋ ነው። ቃየል በወንድሙ በአቤል ክፉን ሀሳብ እና ቅናት አደረበት፣ ክፉ ሀሳብ ገዳይ አጥፉ በመሆኑ ወንድሙን ማጥፋት ችላል፣ ስለዚህ በውሎችን ስንቶቻችን ነን ክፉ ሀሳብ ሲመጣብን ከማስተናገድ ይልቅ የምንቃወመው። እራሳችን መገሰፅ አለብን፣ እንደዚህ ካላደረግን ወደተለያዩ ችግሮች ይዞን ይወርዳል፣ ቃየልን ማየት እንችላለን ክፉ ሀሳቡን ተከትሎ በሰራው ስራ እርሱም ተንከራታች ነው የሆነው። ክፉ ስራ መልካም ያልሆነ ዘር ማለት ነው ተዘርቶ ፍሬው ሲለቀም መልካም ፍሬ ሊሆን አአይችልም። ክፉ ስራ በርቀት ሁነው ሳዩት ፍሬማ ይመስላል ቀርብው ሳዩት ግን ፍሬ አታገኙበትም። ክርስቶስ በለሳን አይቶ በርቀት ሄዶ ፍሬን ሲፈልግ አጣባት፣ ዛፏ የክፋት ዛፍ ስለነበረች ፍሬ አልተገኘባትም።
አስተያየት ያስቀምጡ