ህልም ካለህ ምንም አይነት እንቅፋት አያስቀርህም። ህልማችን ለማሳካት ሌት ቀን የምንደክም ከሆነ አንድ ቀን ህልማችን እውን ይሆናል። በህይወታችን ፈተና የሚጥለው ህልም እይኑረን ግን ፈተናው የበለጠ የሚያጠነክረው፣ የማነሳሳው፣ ዛሬን ሳይሆን ነገን የማሳየው መሆን ነው ያለበት። በዚህ ምድር ህይወት ያለፈተና መንገድ ያለ እንቅፋት አይሆንም። የህይወት ፈተና እንዳይጥልህ እራስህን በደንብ ማጥናት አለብህ፣ ድክመትህን እና ጥንካሬህን ለይተህ ማወቅ። ድክመትህን በአለህ ጠንካራ ጎን ለማጥፋት መሞከር ወይም በጥንካሬህ አንድም ሳይቀር መዋጥ/dominated/ ማድረግ ከዛም በራሱ ጊዜ አንደጨው ማሙቶ ይጠፋል፣ ጥንካሬህ ደግሞ ድክመቶችህን አሳዶ በማጥፋት ታጎለብተዋለህ። ግን ተገላቢጦሽ ከሆነ ደካማው ጎናችን ጠንካራውን ጎናችን የማሳድድ ከሆነ ህልማችን ለማሳካት እንቸገራለን። ስለዚህ ለህልማችን ስኬት ስንል የደካማውን ሹክሹክታ ማዳመጥ የለብነም። ጠንካራውን ጎናችን ልክ እንደመሰላል በመጠቀም ለስኬታችን ግባት ማድረግ እንችላለን።
አስተያየት ያስቀምጡ