የህይወት ምሪት ምንድን ነው? ህይወት እንደፈለገች የምትመራ ግውዝ አይደለችም። በዚህ ምድር ስንመጣ ለምን መጣን፣ እንዴት እንኑር፣ ለምን እንኖራለን እና ምን ሰርተን እንለፍ የሚለው ህይወታችን በጣም ያስጨንቃታል። ህይወት በምታደርገው እጅግ በሚያስጨንቅ ጉዞ ትራመዳለች፣ ሁሌ ህይወት እራሷ መልሱን መመለስ የተሳናት እስኪመስል ድረስ። ህይወት ስልችት ሲል፣ ህይወት ለምን እንደተፈጠረች ምክናቱ ሲጠፋት፣ ብዙ መንገዶችን በመጀመር፣ እንዲሁም ጀምሮ ባለመጨረስ አባዜ ትገባለች። የመጀመር እንጂ የመጨረስ አቋም የሌላት፣ እራሷን በማስጨነቅ፣ ምን ሆኜ ነው ግን የማይሳካልኝ ማለትን ትጀምራለች። ዋናው ምክናቱ ጀምረን ያለመጨረሳችን፣ የኛ የመጣንበትን አላማ ስለማናውቅ ነው። የሰው ልጅ አላማ በምድር ላይ፣ ለራሱ እና ለሰው መኖር ነው። እኛ ግን ለራሳችን ብቻ ስለምንኖር፣ በምንጀምራቸው ማንኛውም ስራችን ማንም ሊረዳን አይችልም፣ ምክንያቱም የሰው ልጅ ሊኖር ከሚገባው አላማ ውጭ እየኖረ ስለሆነ፣ ሰው እኛን ሊረዳን አይችልም። እኛ ለሰው ስለማንኖር፣ ሰውም ለኛ ሊኖር አይችልም። “የሰው ልጅ ብቻውን ይኖር ዘንድ መልካም አይደለም፣ የሚመቸውን እረዳት እንፍጠርለት” በማለት ሰው ለሰው ልጅ ረዳት ለመሆን ተፈጥሮ የነበረ ሲሆን፣ ግን እሁን ላይ ለሰው መኖራችን ትተን፣ ለራሳችን ብቻ ሥለሆነ የምንኖረው፣ የሰው ልጅ ለራሱ ብቻ ከሆነ ለሰው መኖሩን ቸል የምንል ከሆነ፣ የመጣንበትን አላማ ዘነጋን ማለት ነው። በዚህ ምድር ላይ ስንኖር ሳለ ለራሳችን ከመኖራችን በተጨማሪ፣ ለሰው መኖራችን እንዳንዘነጋ። እንደዚህ ካደረግን፣ በምንጀምራቸው ስራዎች ሁሉ ረዳቶቻችን አብረውነ ስለሚሆኑ፣ ህይውታችን በነገሮች ላይ ተስፋ አትቆርጥም።
አስተያየት ያስቀምጡ