በህይወትህ  ልታስወግዳቸው የሚገቡ ነገሮች፣

Published by

on



1: በማይመለከተን ጉዳይ ላይ መግባት፡ በማንኛውም ነገር ላይ ዘው ብሎ መግባት በጣም አደገኛ ጉዳት አለም በሚመጣው ማንኛውም ነገር ተጠያቂ ነው የምንሆነው። በሰውም እይታ ወይም በምትሰሩበት ጅርጅት አስተያየት ወይም አዜኔታም ልታገኙ አትችሉም፡ ስለዚህ ማንኛውን ነገር ለማድረግ ከመውሰናችሁ በፊት እራሳችንን መጠየቅ ያለብን ይህ ነገር እኔን ይመለከታል ወይስ አይመለከተኝም የሚለዉን መሆን አለበት።

2: በጣም በተናደድን ሰሀት አላስፈላጊ ውሳኔዎችን መወሰን፡ በዛ ሠሀት ስሜታችን ትክክል ስላልሆነ የምንወስናቸው ውሳኔዎች ትክክል አይደለም። ብዙ ከማውራት እራሳችን መቆጠብ ምክንያቱም ከኛ አንደበት በወጡት ቃላት ነገ ላይ ማፈር የለብንም።

3: ለተጠየቅነው ጥያቄን በጥያቄ መመለስ። ይህ በጣም አደገኛ ፈፅሞ ከሰው ጋር ሊያግባባን የማይችል ድርጊት ነው። ለተጠየቅነው ጥያቄ አግባብ ያለው መልስ ከሰጠነ በሃላ ጥያቄ ካለነ በተራችን መጠየቅ እንችላለን ግን ጥያቄን በጥያቄ በምንመልስበት ግዜ ጥያቄያቸውን ላለመመለስ የፈለግን ነው የሚመስለው።

4: በተሳሳትከው ነገር ከመማር ይልቅ መፀፀት፡ ሌት ቀን ስለሱ ማሰብ ይህ በህይወታችን ውስጥ በጣም ውስጣችን የሚበዘብዝ ነው። ውድቀት በህይወታችን መማሪያ ነው መሆን ያለበት እንጂ ሁሌም መብሰልሰያ መሆን የለበትም። ላለፈው ነገር በጣም ስናስብ ወደፊት መስራት የሚገባነን በአግባቡ ማከናወን ያቅተናል የሀሳብ መበተን፣ ነገሮችን የመርሳት፣ የያዛችውትን እቃ የመጣል ሁኔታዎች ያጋጥመናል። ያለፈን ነገር አንዴ ትማርበታለህ ከዚያ በኻላ ፈፅሞ ለመርሳት መሞከር ነው።

5: በህይውታችን ልናሥወግዳቸው የሚገቡ ነገሮች፣ በውይይት መግባባት አለመቻል፡ በውይይት ከመግባባት ይልቅ፡ በጉልበት፣ በሀይለቃል፣ በማስፈራራት፣ አንድን ነገር ለማስረዳት እና ለማሳመን መሞከር በአላስፈላጊ ሁኔታ አንድን ሰው ለማሳመን በምትሞክሩበት ጊዜ ያ መተማመን ሳይሆን ተገዶ ሳይፈልገው አንድን ነገር እንዲቀበል ስላደረጋችሁት  ነገ ላይ የራሱን አቐም ነው ሊያራምድ የሚችለው። የአንተን ሀሳብ ሊቀበል የሚችለው ምክናታዊ በሆነ መልኩ ስታስረዳው ያልገባውን ነገሮች ሲጠይቅህ ስትመልስለት እና ከርሱም የሚመጡትን ሀሳቦች ተቀብለህ በጉዳዩ ላይ ተሳታፊ ሲሆን፡ መድረኩን ክፍት ስታደርገው እና አንተው ሀሳቡን አምተህ አንተው ብቻ ሳትዘጋ፡ ለሁሉም የአንተን ሀሳብ እንዲቀበሉት በቂ የሆኑ ምክንያቶች በበቂ ማስረጃ ዎች ስታስረዳና ሁሉም አመኔታ ሲሰጥህ መሆን አለበት። 

6: በህይውታችን ልናሥወግዳቸው የሚገቡ ነገሮች ብዙ ስራዎችን ወይም እቅዶችን በአንዴ ለመስራት መሞከር፣ አንድን ነገር ለመስራት ካሰብን እርሱን ሳንጨርስ ሌላ በምንጀምርበት ጊዜ የአንድን ነገር ጀምሮ የመጨረስ አቅማችን እየደከመ ነው የሚሄደው፡ በዚህ ጊዜ ሥራዎችን በተሳካ ሁኔታ ማከናወን ያቅተናል። በዚህ የተነሳ ብዙ ነገሮችን እናባክናለን፣ ጉልበታችን፣ ጊዜአችን፣ ገንዘባችን፣ ልናከናውን በማንችላቸው ነገሮች ላይ ልናባክን እንችላለን 

7:ችግርህን ከማይረዳህ ወይም ከማይገነዘብ ሰው ላይ
መፍትሄን መፈለግ፡  አንድን ሰው ለማስረዳት ሁኔታዎችን በሚገባው ቐንቐ ልታስረዳው ስትሞክር፡ ግን እርሱ ሊረዳህ ካልቻለ፡ ሊረዳህ ያልቻለበት ምክኒያት፡ የአንተ ነገር ግድ የማይለው ሆኖ፡ ወይም እንዳይረዳህ ያደረገው የራሱ ችግር ቢኖርበት ነው፡ በዚያ ሰሀት እያወቀ ግን ልክ እንዳልተረዳህ መስሎ ላልፍ ይችላል፡ ስለዚህ በዛ ሰሀት ከዛ ሰው ጋር መፍትሄን በመፈለግ ብዙም ግዜ ማጥፋት የለብህም። 

አስተያየት ያስቀምጡ

Discover more from Edudream Family Community

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading